Raise Act

Book a Consultation
100% Secure & Confidential
★★★★★
100+ Reviews

በፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊነት ስለቀረበውና“ለጠንካራ ኢኮኖሚ ሲባል የአሜሪካን ኢሚግሬሽን ስለማሻሻል የወጣ ሕግ” (The Reforming American Immigration for a Strong Economy Act ወይም በምሕጻረ ቃልRAISE Act) በመባል ስለሚታወቀው የሕግ ማሻሻያ የቀረበ አጭር ማብራሪያ::

የዳይቨርሲቲ ቪዛ(ዲቪ) ፕሮግራም

 • የዲቪ ፕሮግራም እንዲኖር ያደረገውን የኢሚግሬሽን እና የዜግነት ሕግ አንቀጽ በማስቀረት ሬይዝ አክት ለብዙ ኢትዮጵያዊያን ወደ አሜሪካ መምጫ መንገድ የሆነውን ዲቪን ያስወግዳል። ይህም ተፈጻሚ የሚሆነው በረጅም ጊዜ እቅድ (ለምሳሌ በ5 ወይም በ10 ዓመታት ውስጥ) ሳይሆን ወዲያውኑ ማለትም ሬይዝ አክት ተፈጻሚ በሚሆንበት ቀን ወይም ከዚያ በኋላ ባለው የመጀመሪያ የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ቀን ነው፡፡

ስደተኞች

 • ሬይዝ አክት በማንኛውም የበጀት ዓመት ሊገቡ የሚችሉትን ስደተኞች ከፍተኛ ቁጥር 50,000 አድርጎ ገድቧል እንዲሁም ፕሬዚደንቱን ‹‹በቀደመው የበጀት ዓመት ጥገኝነት የተፈቀደላቸውን የውጭ ዜጎች ቁጥር በየዓመቱ እንዲያስቀምጡ›› ያስገድዳል፡፡

በቤተሰብ ግንኙነት ላይ የተመሠረተ ኢሚግሬሽን የ‹‹ልጅ›› እና የ‹‹ቅርብ ቤተሰብ›› ትርጓሜዎች ስለመቀየራቸው

 • በኢሚግሬሽን እና ዜግነት ሕግ ላይ የነበረው የ‹‹ልጅ›› ትርጓሜ ማለትም ‹‹ከ21 ዓመት እድሜ በታች የሆነ/ችና ባለትዳር ያልሆነ/ች” የሚለውን ሬይዝ አክት ‹‹ከ18 ዓመት እድሜ በታች የሆነ/ችና ባለትዳር ያልሆነ/ች›› በሚል ወደ አሜሪካ መጥቶ መኖር የሚቻልበትን የልጅ እድሜ ገደብ በመቀነስ ቀይሮታል፡፡
 • ሬይዝ አክት በኢሚግሬሽን እና ዜግነት ሕግ ላይ በ‹‹ቅርብ ቤተሰብ›› ትርጓሜ ውስጥ የሚካተቱትን የቤተሰብ አባላት ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ያላገቡ ልጆችን እና የትዳር ጓደኞችን ብቻ በማድረግ የአሜሪካ ዜጋ ልጆችን ወላጆች የአሜሪካ ነዋሪ የመሆን አማራጭ አስወግዷል፡፡

በቤተሰብ ግንኙነት ላይ በተመሠረተው የኢሚግሬሽን ስርዓት ላይ የተደረጉ ለውጦች

 • ዓለም አቀፍ ገደቦች
  • በዓለም አቀፍ ደረጃ በቤተሰብ የድጋፍ ተጠሪነት ለመኖር ወደ አሜሪካ የሚገቡ የሌሎች አገሮች ዜጎችን (immigrants) በሚመለከት ሬይዝ አክት አዲስ የኢሚግሬሽን እና የዜግነት ሕግ አንቀጽ 201(ሐ)ን [(INA §201(c))ን] በማከል በቤተሰብ ግንኙነት ላይ የተመሰረቱ ቅበላዎችን ከፍተኛ ቁጥር በየበጀት አመቱ ከ88,000 እንዳይበልጥ አድርጎ ገድቧል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በተለያየ አጋጣሚ በጊዜያዊ አመክሮ እንዲገቡ የተፈቀደላቸው ሰዎች ከአገር ካልወጡ ወይም ከዚህ የቁጥር ገደብ ውጭ በሆነ አኳኋን የቋሚ ነዋሪነት ፈቃድ ካላገኙ የእነርሱ ቁጥርም ከዚሁ የተገደበ ቁጥር ላይ ይቀነሳል፡፡ ስለሆነም ሬይዝ አክት በየበጀት ዓመቱ ወደ አሜሪካ እንዲገቡ የሚፈቅደው ከቁጥር ገደቡም ያነሰ ቁጥር ያላቸውን በቤተሰብ የድጋፍ ተጠሪነት የሚመጡ ሰዎችን ሊሆን ይችላል፡፡
 • በቤተሰብ ላይ የተመሠረተ የምርጫ ስርዓት
  • ሬይዝ አክት የቋሚ ነዋሪነት ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ለትዳር ጓደኞቻቸው እና ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ያላገቡ ልጆቻቸው ብቻ ማመልከት እንዲችሉ ያደርጋል። ይህም ማለት ከ18 ዓመት በላይ ሆነው ላላገቡ ልጆቻቸው ማመልከትን የከለክላል።
  • ይህ ብቻ ሳይሆን ሬይዝ አክት የአሜሪካ ዜጎችን ያላገቡ ልጆች (FB-1)፣ የሕጋዊ ቋሚ ነዋሪዎችን ያላገቡ ልጆች (FB-2B)፣ የአሜሪካ ዜጎችን ያገቡ ልጆች (FB-3)፣ እና የአሜሪካ ዜጎችን ወንድሞች እና እህቶች (FB-4) በሙሉ በቤተሰብ ላይ በተመሠረተ የምርጫ ስርዓት መሠረት ወደ አሜሪካ ገበተው ነዋሪ እንዳይሆኑ ይከለክላቸዋል፡፡
 • የአሜሪካ ዜጋ ለሆኑ ልጆች ወላጆች የሚሰጥ የተለየ ጊዜያዊ ለነዋሪነት ቋሚ ያልሆነ (nonimmigrant) ፍረጃ
  • 21 ዓመት ለሞላቸውና የአሜሪካ ዜግነት ላላቸው ልጆች ወላጆች አዲስ ቋሚ ያልሆነ ፍረጃ (W) ፈጥሯል፡፡
  • መሰረት፡-
   • ለ5 ዓመት መነሻ የፈቃድ ጊዜ ይሰጣል፤ ይህም ቪዛ ለተጨማሪ 5 ዓመት ጊዜ ይታደሳል
   • እነኚህ ወላጆች መስራት አይችሉም
   • እነኚህ ወላጆች የሕክምናም ሆነ ምንም ዓይነት የመንግስት ድጋፍ አያገኙም
   • ወደ አሜሪካ እንዲመጡ የጋበዟቸው አሜሪካዊ ልጆች ለእነኚህ ወላጆቻቸው የግዴታ የጤና ኢንሹራንስ እንዲሁም ሙሉ ዋስትና ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

እጅግ አሳሳቢ የሆነው ጉዳይ ደግሞ የሬይዝ አክት ሕግ ሆኖ ከመውጣቱ በፊት ከገቡ ማመልከቻዎች መካከል በ1 ዓመት ጊዜ ውስጥ ቋሚ የመኖርያ ፈቃድ የማግኘት ወረፋቸው ከደረሱት በስተቀር ሌሎቹን በሙሉ በመሻር ያስወግዳቸዋል፡፡ በነጥብ ላይ የተመሰረተ ኢሚግሬሽን በሥራ ቅጥር ላይ የተመሠረቱ የኢሚግሬሽን ፍረጃዎች በነጥብ ላይ በተመሠረተ ሥርዓት ስለመተካታቸው

 • ሬይዝ አክት (የትዳር ጓደኞችን እና ልጆችን ጨምሮ) በነጥብ ላይ የተመሠረቱ ስደተኞችን ቁጥር 140,000 ወይም በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ውስጥ 70,000 አድርጎ ይገድባል።

ነጥቦች የሚቆጠሩት

 1. ዕድሜ

0-17 ማመልከት አይችልም 18-21 6 ነጥብ 22-25 8 ነጥብ 26-30 10 ነጥብ 31-35 8 ነጥብ 36-40 6 ነጥብ 41-45 4 ነጥብ 46-50 2 ነጥብ

 1. በላይ 0 ነጥብ
 1. ትምህርት
  • አገር ሁለተኛ ደረጃ 1 ነጥብ
  • አገር ባችለር ዲግሪ 5 ነጥብ
  • ባችለር ዲግሪ 6 ነጥብ
  • STEM ዲግሪ 7 ነጥብ
  • STEM ዲግሪ 8 ነጥብ
  • ዶክትሬት 10 ነጥብ
  • ዶክትሬት 13 ነጥብ
 1. የእንግሊዝኛ ችሎታ በ TOEFL ወይም IELTS የሚለካ

1-5 th Decile 0 ነጥብ

 1. ነጥብ
 2. ነጥብ
 3. ነጥብ

10 Decile 12 ነጥብ

 1. ረቂቅ የሆነ ችሎታ
  • ተሸላሚ 25 ነጥብ
  • ተሸላሚ 15 ነጥብ
 2. ሥራ ያገኘ
  • ካገኘበት አካባቢ ደመወዙ 150—250% በላይ ከአካባቢው አማካይ ደመወዝ ከሆነ 5 ነጥብ
  • ካገኘበት አካባቢ ደመወዙ 200—300% በላይ ከአካባቢው አማካይ ደመወዝ ከሆነ 8 ነጥብ
  • ካገኘበት አካባቢ ደመወዙ 300% በላይ ከአካባቢው አማካይ ደምወዝ ከሆነ 13 ነጥብ
 3. የበርካታ ካፒታል ኢንቨስትመንት
  • $1.35 ሚሊዮን ብር በላይ ቢያንስ ለ 3 ዓመት ሥራውን እራሱ እየመራ አዲስ ሥራ ላይ ካዋለ 6 ነጥብ
  • $1.8 ሚልዮን ብር በላይ ቢያንስ ለ 3 ዓመት ሥራውን እራሱ እየመራ አዲስ ሥራ ላይ ካዋለ 12 ነጥብ
 4. በቤተሰብ ፍርጃ የቪዛ ማመልከቻ
 5. በተጠቀሰው መስረት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ቪዛ ሊያገኝ ሲገባ ያላገኘ እስከ 2 ነጥብ ያገኛል

የዜግነት መስፈርት

 • ከመንግስት ማንኛውንም ዓይነት ጥቅማ ጥቅም ያገኘና ያንንም ለመንግስት መልሶ ያልከፈለ ማንኛውም ሰው የአሜሪካ ዜግነት ማግኘት አይችልም፡፡
Available 24/7
408-292-7995

Get Help Today

Our team of experienced immigration attorneys are ready to answer your questions.

"*" indicates required fields

This field is for validation purposes and should be left unchanged.