በአሁኑ ጊዜ መሰረታዊ የሆኑ ማንም ሊያውቅቸው የሚገቡ መብትና ግዴታዎች-መብታችንን እንወቅ
- ለቤት ሳንቃ ለነገር ጠበቃ
የኢሚግሬሽን መኖሪያ አማራጮችዎን ከአሁኑ የኢሚግሬሽን ጠበቃዎችን ወይንም የአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ያነጋግሩ አቅም ካልዎት ከፍለው በተለይም በ አሜሪካን ኢሚግሬሽን ጠበቆች ማህበር አባል የሆኑና እውቀት ያላቸውን ጠበቆች ያማክሩ፡፡ የመክፈል አቅም ከሌለዎት ደግሞ በነፃ ወይም በአነስተኛ ክፍያ የኢሚግሬሽን ሕግ ድጋፍ አገልግሎት የሚሰጡ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን አገር አቀፍ ስም ማውጫ (ዳይሬክትሪ) በያዘው የኢሚግሬሽን ጠበቆች ቅንጅት (Immigration Advocates Network) https://www.immigrationlawhelp.org ላይ የኢሚግሬሽን ሕግ እገዛ ያግኙ፤ በተለይም ሊያውቁ የሚገባዎት
- አረንጓዴ ካርድ ካለዎት የአሜሪካ ዜጋ ለመሆን መቻል አለመቻልዎን፤
- አሜሪካ ያሉት በቪዛ ከሆነ አረንጓዴ ካርድ ለማግኘት መቻል አለመቻልዎን፤
- ምንም ዓይነት የኢሚግሬሽን ሁኔታ (status) ከሌለዎት ቪዛ ወይም የሥራ ፈቃድ ለማግኘት መቻል አለመቻልዎን፤
- በወንጀል ተይዘው ወይም ተፈርዶብዎ ከሆነ ይህ እውነታ በጉዳይዎ ላይ ምን ዓይነት ተጽእኖ ሊኖረው እንደሚችል ወይም ከመዝገብዎ ሊፋቅ የሚችልበት መንገድ መኖር አለመኖሩን ፡፡
- ታሞ ከመማመቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ-
- ጥበቃ እና የቤተሰብ ዝግጁነት እቅድ ያውጡ
- ልጆችዎን ማን ከትምህርት ቤት ለማውጣት እንደሚችልና እንደማይችል ያለውን መረጃ ጨምሮ በልጆችዎ ትምህርት ቤት/ቤቶች የተመዘገቡት ሁሉም መረጃዎች እና የአደጋ ጊዜ ተጠሪ ሰዎች ለአሁኑ ጊዜ ወቅታዊ መደረጋቸውን ያረጋግጡ፤
- የአደጋ ወይም የአስቸኳይ ጊዜ ስልክ ቁጥሮችን እና አድራሻዎችን ዝርዝር ጽፈው በማዘጋጀት እና ጠቃሚ ሰነዶችን ፋይል በማድረግ እርስዎ፣ የቤተሰብዎ አባላት ወይም ለአደጋ ጊዜ ለእርስዎ ተጠሪ የሆነው ሰው በቀላሉ ልታገኟቸው እንድትችሉ ያድርጉ፤
- የተሟላ የመደበኛ አጋዥ ፈቃድ መስጫ ቃለ መሃላ (caregiver’s authorization affidavit) በማሟላት ሌላ አዋቂ ሰው ልጆችዎን ለጊዜው ለመያዝ እንዲችሉ ያድርጉ (ይህ አማራጭ በካሊፎርኒያ በሥራ ላይ ያለ ነው)፤
- ልጅዎ አሜሪካ የተወለደ/የተወለደች ከሆነ የልጅዎን መወለድ በአገርዎ መንግስት ያስመዝግቡ (ለምሳሌ በአገርዎ ቆንሱል)፡፡
- በእጅ የያዙት ወርቅ ከመዳብ እኩል ነው
አሜሪካ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የትኞቹን ሰነዶች መያዝ እንዳለብዎት እና እንደሌለብዎት ይወቁ
- ተገቢው የሥራ ፈቃድ ወይም አረንጓዴ ካርድ ካለዎት ሁልጊዜም ይያዙት፡፡ ከሌለዎት ደግሞ በአሜሪካ ውስጥ የተሰጠዎት እና ስለ ኢሚግሬሽን ሁኔታዎም ሆነ ስለትውልድ አገርዎ ምንም ዓይነት መረጃ ያልያዘ መታወቂያ፣ የአሜሪካ ግዛት (ስቴት) መታወቂያ ወይም መንጃ ፈቃድ መያዝ በአጠቃላይ ይመከራል፡፡ ባሉበት ቦታ ምን ዓይነት ሰነዶችን መያዝ ችግር እንደማያስከትል ለማወቅ በአካባቢዎ ያለ/ያለች የኢሚግሬሽን ጠበቃ ይጠይቁ፤
- የትውልድ አገርዎን የሚመለከት ምንም ዓይነት ሰነድ አይያዙ፤
- ምንም የሀሰት የማንነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ወይም የሀሰት የኢሚግሬሽን ሰነዶችን አይያዙ፤
- የኢሚግሬሽንና የጉምሩክ አስፈጻሚ (አይ.ሲ.ኢ ወይም ICE) ወይም ፖሊሶች ቢያሰቆሙዎት ወይም ጥያቄ ቢጠይቁዎት መልስ ባለመስጠት በዝምታ የመቆየት መብትዎትን ለመጠቀም በማንኛውም ጊዜ ቀይ ካርድ ይያዙ፡፡
የኢሚግሬሽን ድንገተኛ ዱብዕዳ ሲገጥም ሁሉም ሰዎች ያላቸው መብቶች
- ዝምታ ወርቅ ነው-ዝምታ መብት ነው
ሁሉም ሰዎች- የመኖሪያ ሰነድም ይኑራቸው አይኑራቸው – በአሜሪካ ውስጥ መብቶች አሏቸው፡፡ የአይ.ሲ.ኢ ሠራተኞች ወደ እርስዎ ቢመጡ ምን እንደሚደረግ ይወቁ ሌሎችንም ያሳውቁ፡፡ የአይ.ሲ.ኢ. ሠራተኞች ወይም ፖሊሶች ወደ ቤትዎ፣ ሰፈርዎ ወይም የሥራ ቦታዎ ቢመጡ የኢሚግሬሽን ሁኔታቸው ምንም ይሁን ምን ህጻናትን ጨምሮ የቤተሰብዎን አባላት፣ በቤትዎ አብረው የሚኖሩ ሰዎችን፣ ጎረቤቶችዎንና የሥራ ባለደረቦችዎን ሳይናገሩ በዝምታ የመቆየት መብትን እንዲሁም እነዚህን መብቶቻቸውን በሙሉ በሚመለከት እንዲያውቁ ያድርጉ፡፡ Ü ባለመናገር በዝምታ የመቆየት መብት አለዎት፤ የአይ.ሲ.ኢ ወኪልን አላናግርም የማለት መብት አለዎት፡፡ በተለይም የትውልድ ቦታዎትን፣ የኢሚግሬሽን ሁኔታዎትን ወይም ወደ አሜሪካ የገቡበትን መንገድ በሚመለከት ምንም ጥያቄ አይመልሱ፡፡ ጠበቃ እስከሚያናግሩ ድረስ ባለመናገር በዝምታ መቆየት እንደሚፈልጉ ይግለጹ፡፡ Ü ማንኛውንም ሰው ወደ ቤትዎ ከማስገባትዎ በፊት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ስለመኖሩ የመጠየቅ መብት አለዎት፤ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለመጡ ባለሥልጣናት በርዎን አይክፈቱ፡፡ የአይ.ሲ.ኢ. ወኪሉ/ወኪሏ በፍርድ ቤት ዳኛ የተፈረመ የእርስዎ ትክክለኛ ስም እና አድራሻ የሰፈረበት ትዕዛዝ ካላሳየዎት/ካላሳየችዎት በስተቀር በርዎን መክፈት አያስፈልግዎትም፡፡ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለን ካሉዎት ትዕዛዙን እንዲያሳዩዎት በሩን አይክፈቱ፡፡ በበሩ ስር ወይም በመስኮት በኩል እንዲያሳልፉት ይጠይቋቸው፡፡ Ü ጠበቃ የማማከር እና ስልክ የመደወል መብት አለዎት፤ Ü ጠበቃ ከማማከርዎ በፊት ምንም ነገር አልፈርምም የማለት መብት አለዎት፤ ምንም ነገር አይፈርሙ፡፡ መፈረም ጠበቃ የማማከር መብትዎን ወይም በኢሚግሬሽን ዳኛ ፊት ቀርበው የመሰማት መብትዎን ሊያሳጣዎት ይችላል፡፡ ይህም ጉዳይዎ ሳይሰማ ወዲያውኑ ከአገር እንዲወጡ የመደረግ ውጤት ሊያሰከትልብዎ ይችላል፡፡ Ü ጠበቃ ከማማከርዎ በፊት ምንም ዓይነት ሰነድ አላሳይም የማለት መብት አለዎት፡፡
በአጠቃላይ ለማህበረሰቡ የምንመክረው ያለደህንነት ስጋት ማድረግ የሚችሉ ከሆነ ምስሎችን (ፎቶዎችን)፣ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን (ቪዲዮዎችን) እና ሰነዶችን ይቅረጹ እንዲሁም ወረራዎቹን እና መያዞቹን (arrests) ይጠቁሙ፡፡
- የማናቸውንም ምስክሮች ስሞች እና ስልክ ቁጥሮች ይያዙ፤
- ከሥራ ባልደረቦችዎ ጋር ወረራውን በሚመለከት መረጃ ይለዋወጡ፡፡ በሚሰሩበት ቦታ የሠራተኞች ማህበር ካለ የማህበሩን ሠራተኛ ወይም ተወካይ ያግኙ፡፡
- የአይ.ሲ.ኢ. ወኪሎች ወይም ፖሊሶች ያለ ተገቢ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ገብተው ከሆነ ስማቸውን ይጠይቁ እና/ወይም የባጅ ቁጥራቸውን ይጻፉ፡፡
Ü የተፈጸመን የኢሚግሬሽን ወረራ ለመጠቆም የዩናይትድ ዊ ድሪምን ቀጥታ መስመር 18443631423 በስልክ ያግኙ ወይም 877877 ላይ የጽሑፍ መልዕክት ይላኩ፡፡
- በአይ.ሲ.ኢ.፣ በፖሊስ ወይም በጠረፍ ጠባቂዎች የሚፈጸሙ ወረራዎችን ወይም ጥቃቶችን/ወከባዎችን ይጠቁሙ፡፡